ሕክምናHikimna · Amharic health reference
ለትምህርት ብቻ ነው። Educational only.

የእንቅልፍ እጥረት፦ በአእምሮና በሰውነት ላይ የሚያመጣው ጉዳት

Not getting enough sleep: effects on the mind and body

ቪዲዮ · Dr. Sofonias Ermias

ጽሑፍ፦ ሕክምና · Prepared by Hikimna · 2026-10-21

ምንድን ነው?

የእንቅልፍ እጥረት (sleep deprivation) በቂ ሰዓት አለመተኛት ወይም ጥራት የሌለው እንቅልፍ መተኛት ነው። ለአንድ ሌሊት ሲሆን ድካም ያመጣል። በየጊዜው ሲደጋገም ግን አእምሮንም ሰውነትንም ይጎዳል።

በእንቅልፍ ጊዜ ሰውነት ልብንና የደም ሥሮችን ያድሳል፣ የበሽታ መከላከያን ይደግፋል፣ አእምሮ ደግሞ የተማረውን ያደራጃል። ስለዚህ እንቅልፍ ቅንጦት ሳይሆን የጤና አስፈላጊ ክፍል ነው።

አዋቂዎች በሌሊት ከ7 እስከ 9 ሰዓት መተኛት ይመከራል። ከ7 ሰዓት በታች በየጊዜው የሚተኙ ሰዎች ብዙ የጤና ችግሮች ሊገጥሟቸው ይችላሉ። ልጆችና ወጣቶች ከዚህ የበለጠ ያስፈልጋቸዋል።

አደገኛ ምልክቶች

ከሚከተሉት አንዱ ካለ ወዲያውኑ እርዳታ ይፈልጉ፦

  • ራስዎን የመጉዳት ወይም የማጥፋት ሀሳብ ከመጣ።
  • እየነዱ ወይም ማሽን እያንቀሳቀሱ እንቅልፍ ቢያሸንፍዎት፤ መንዳቱን ወዲያውኑ ያቁሙ።
  • ሲተኙ ትንፋሽዎ ሲቆም እንደሚታይ ቤተሰብ ቢነግርዎ፣ ከብርቱ ማንኮራፋት ጋር።

በአሜሪካ 911 ይደውሉ። በአዲስ አበባ የቀይ መስቀል አምቡላንስ 907 ነው፤ በሌሎች ቦታዎች የአካባቢውን የድንገተኛ አገልግሎት ያነጋግሩ።

ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?

  • በየቀኑ፣ በዕረፍት ቀንም ጭምር፣ በተመሳሳይ ሰዓት ይተኙ፤ በተመሳሳይ ሰዓት ይነሱ።
  • መኝታ ቤቱን ጨለማ፣ ጸጥ ያለና ቀዝቃዛ ያድርጉት። መጋረጃ ይዝጉ፤ ስልክዎን ከእይታ ያርቁ።
  • ከሰዓት በኋላ ቡናና ሌሎች ካፌይን ያላቸውን መጠጦች ይቀንሱ።
  • ከመተኛትዎ በፊት ከ1 እስከ 2 ሰዓት አልኮልና ሲጋራ ያስወግዱ፤ ከመተኛት ጥቂት ቀደም ብሎ ከባድ ምግብ አይብሉ።
  • ቀን ላይ በየጊዜው የአካል እንቅስቃሴ ያድርጉ፤ እንቅልፍን ያሻሽላል።
  • እንቅልፍ ካልመጣ በአልጋ ላይ ተገላብጠው አይቆዩ፤ ተነስተው ጸጥ ያለ ነገር ያድርጉ፣ እንቅልፍ ሲመጣ ይመለሱ።
  • ያለ ሐኪም ምክር የእንቅልፍ መድኃኒት አይውሰዱ።
ምልክቶች
  • ትኩረት ማጣት፣ የማስታወስና ውሳኔ የመስጠት ችግር።
  • ቶሎ መበሳጨት፣ የስሜት መለዋወጥ፣ ሀዘን ወይም ድብርት (depression)።
  • ቀኑን ሙሉ የድካም ስሜትና የጉልበት ማነስ፤ በተለይ ከሰዓት በኋላ።
  • ሥራ የመሥራት ፍላጎት መቀነስ።
  • በተደጋጋሚ በበሽታ መያዝ፤ የበሽታ መከላከል አቅም ሊቀንስ ይችላል።
  • ቀን ላይ ሳያስቡት ማንቀላፋት።
ሐኪም መቼ ማየት?
  • ለሳምንታት እንቅልፍ ለመተኛት ወይም ተኝተው ለመቆየት ከተቸገሩ።
  • በቂ ሰዓት ተኝተውም ቀን ላይ በጣም ከደከሙ ወይም ካንቀላፉ።
  • በብርቱ የሚያንኮራፉ ከሆነ ወይም ትንፋሽዎ ሲቆም ከታየ፤ የእንቅልፍ አፕኒያ (sleep apnea) ሊሆን ይችላል።
  • የእንቅልፍ እጥረቱ ከድብርት፣ ከጭንቀት ወይም ከሕመም ጋር ከተያያዘ።
መከላከያ
  • እንቅልፍን እንደ ምግብና ውሃ የቀን ዕቅድዎ አካል ያድርጉት።
  • ከመተኛት በፊት ስልክና ቴሌቪዥን ይቀንሱ።
  • የደም ግፊትዎን፣ ክብደትዎንና ስኳርዎን በየጊዜው ያስለኩ።
  • የፈረቃ ሥራ ካለ ቀን ሲተኙ ክፍሉን ጨለማ ያድርጉ።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
  • የእንቅልፍ ችግሬ ምክንያት ምን ሊሆን ይችላል?
  • የእንቅልፍ ምርመራ (sleep study) ያስፈልገኛል?
  • የምወስዳቸው መድኃኒቶች እንቅልፌን ይነካሉ?
  • ያለ መድኃኒት እንቅልፌን ለማሻሻል ምን ማድረግ እችላለሁ?
ምንጮች
  • https://www.nhlbi.nih.gov/health/sleep-deprivation/health-effects
  • https://www.nhlbi.nih.gov/health/sleep/how-much-sleep
  • https://www.nhs.uk/every-mind-matters/mental-wellbeing-tips/how-to-fall-asleep-faster-and-sleep-better/

ጥያቄዎችና መልሶች

የመጀመሪያውን ጥያቄ ይጠይቁ።

ጥያቄዎ ከታየ በኋላ እዚህ ይወጣል። · Your question appears after it is checked.

ተያያዥ ርዕሶች

ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን