ቡናና ካፊን በሰውነታችን ውስጥ
Coffee and caffeine in the body
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ · Reviewed by a medical professional · 2026-09-20
ምንድን ነው?
ካፊን (caffeine) በቡና ውስጥ በተፈጥሮ የሚገኝ፣ ንቁ እንድንሆን የሚያደርግ ኬሚካል ነው። ቡና ብቻ አይደለም፤ ሻይ፣ አንዳንድ ሶዳ፣ ኤነርጂ ድሪንክ (energy drink)፣ ቸኮሌትና አንዳንድ የራስ ምታት መድኃኒቶችም ካፊን አላቸው። ሰውነታችን የሚሰማው ከየት እንደጠጣን ሳይሆን፣ በቀን…
አደገኛ ምልክቶች
- የደረት ሕመም ወይም መጨናነቅ፣ በተለይ ወደ ክንድ፣ መንጋጋ ወይም ጀርባ ሲሰራጭ።
- ትንፋሽ ማጠር፣ ወይም ራስ መሳት።
- ልብ በጣም ፈጥኖ ወይም ያልተስተካከለ ምት እየመታ፣ ከእሱ ጋር ማዞር ወይም ድክመት።
ቤት ውስጥ
- ለጥቂት ቀናት ምን እንደጠጡ፣ መጠኑን፣ ሰዓቱንና እንዴት እንደተኙ ኖት ያድርጉ። ቡና ብቻ ሳይሆን ሻይ፣ ሶዳ፣ ኤነርጂ ድሪንክና መድኃኒትም ይቁጠሩ።
- እንቅልፍዎ ከተረበሸ የመጨረሻውን ቡና ቀደም ብለው ይጠጡ፣ መጠኑንም ይቀንሱ። ከመተኛትዎ ቢያንስ ስድስት ሰዓት በፊት ቡና፣ ሻይና አልኮል ማቆም ይመከራል። NHS።
- ሲኒ መቁጠር ብቻ አይበቃም። ትንሽ የጀበና ሲኒ፣ ትልቅ ቴክአዌይ ኮፊና ኤስፕሬሶ ተመሳሳይ መጠን የላቸውም። ለአብዛኞቹ ጤናማ አዋቂዎች በቀን እስከ 400 ሚሊግራም (mg) ካፊን በአጠቃላይ ከጎጂ ተጽእኖ ጋር አይያያዝም፤ ግን ይህ ለሁሉም ዋስትና ወይም የሚደረስበት ታርጌት አይደለም። ከዚያ በታችም ችግር ሊሰማዎት ይችላል። FDA።
- የሚገዙትን መጠጥ ሌብል ይመልከቱ። ዲካፍ (decaf) ቡናም ትንሽ ካፊን አለው።
- ናይት ሽፍት የሚሠሩ ከሆነ፣ ካፊኑን በሽፍቱ መጀመሪያ ክፍል ይውሰዱ። ሽፍቱ ሊያልቅ ሲል የሚጠጡት ኮፊ ቤት ደርሰው ሲተኙ አብሮዎት ይቀጥላል።
- ካፊንን ለመቀነስ ከፈለጉ፣ ድንገት ከማቆም ይልቅ ቀስ በቀስ መቀነስ የዊዝድሮዋል ጊዜውን ሊያቀለው ይችላል።
- አልኮል ከጠጡ በኋላ ቡና መጠጣት አልኮሉን ከደምዎ አያስወግድም። የነቁ ሊመስልዎት ይችላል፣ ግን ለመንዳት ሴፍ አያደርግዎትም። CDC።
ምልክቶች
ካፊን የሚያደርገው፣ በተለይ ከለመዱት በላይ ሲወስዱ፦
- ንቃትና ኮንሰንትሬት (concentrate) ማድረግ መቀለል፤ ከመጠን ሲያልፍ መረበሽ፣ የእጅ መንቀጥቀጥና አንክሳይቲ (anxiety)።
- ልብ ቶሎ ቶሎ መምታት፣ የደም ግፊት (blood pressure) ለጊዜው መጨመር።
- የጨጓራ አሲድ መጨመር፤ ሆድ መረበሽ ወይም ቃር (heartburn)።
- ሽንት መብዛት።
- መተኛት መቸገር፣ የእንቅልፍ ቆይታና ኳሊቲ መቀነስ። ተጽእኖው ከጠጡ በኋላ ለአራት እስከ ስድስት ሰዓታት ሊቀጥል ይችላል። MedlinePlus።
- በየቀኑ የሚጠጡ ሰዎች ድንገት ሲያቆሙ፣ ራስ ምታት፣ ድካም፣ እንቅልፍ፣ መበሳጨትና ማቅለሽለሽ ሊመጣ ይችላል። ይህ ዊዝድሮዋል (withdrawal) ነው፤ አደገኛ አይደለም፣ በአብዛኛው በጥቂት ቀናት ይጠፋል። FDA።
ሐኪም መቼ ማየት?
- የልብ ምት ችግር ደጋግሞ የሚመጣ ከሆነ፣ ቡና ነው ብለው ብቻ አይተዉት፤ ያስመርምሩ።
- የደም ግፊት፣ የልብ ምት መዛባት (arrhythmia)፣ ቃር ወይም አልሰር (ulcer)፣ ማይግሬን (migraine)፣ አንክሳይቲ፣ ወይም የእንቅልፍ ችግር ካለብዎ፣ ምን ያህል ካፊን እንደሚስማማዎት ሐኪም ያማክሩ።
- አንዳንድ መድኃኒቶች (ስቲሙላንት፣ አንዳንድ አንቲባዮቲክ፣ የአስም እና የልብ መድኃኒቶች) ከካፊን ጋር ሊገናኙ ይችላሉ። የሚወስዱትን ሁሉ ለሐኪምዎ ይንገሩ። MedlinePlus።
- ቡና ቀንሰውም እንቅልፍዎ ካልተስተካከለ፣ ሌላ ምክንያት ሊኖር ስለሚችል ያስመርምሩ። ሁሉም የእንቅልፍ ችግር ከቡና አይመጣም።
መከላከያ
- የቀኑን ጠቅላላ ካፊን ከሁሉም ምንጮች ያስቡ፣ ሲኒ ብቻ አይቁጠሩ።
- እርጉዝ ከሆኑ 400 ሚሊግራምን እንደ መመሪያ አይውሰዱ። በእርግዝና ከሁሉም ምንጮች በቀን ከ200 ሚሊግራም (mg) በላይ ካፊን አይውሰዱ፤ ከመጠን በላይ ካፊን ከውርጃና ከሞተ ልጅ መወለድ ስጋት ጋር ተያይዟል። NHS።
- ጡት እያጠቡ ከሆነ፣ ትንሽ ካፊን ወደ ልጁ ስለሚያልፍ፣ የሚስማማዎትን መጠን ከሐኪም ጋር ይወያዩ።
- የአዋቂዎችን መጠን ለልጆች አይጠቀሙ። ለልጆችና ለቲኔጀሮች ኤነርጂ ድሪንክ አይሰጥም። FDA።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- በጤናዬና በመድኃኒቶቼ ምክንያት ካፊን መቀነስ አለብኝ?
- የልብ ምቴ ወይም የደም ግፊቴ ከቡና ጋር ይያያዛል፣ ወይስ ሌላ ምክንያት አለው?
- እርጉዝ ወይም ጡት አጥቢ ስሆን፣ ለእኔ የሚስማማው መጠን ምን ያህል ነው?
- የእንቅልፍ ችግሬ ከቡና ብቻ ነው፣ ወይስ ሌላ ምርመራ ያስፈልገኛል?
ምንጮች
- FDA. Spilling the Beans: How Much Caffeine is Too Much?
- MedlinePlus. Caffeine.
- NHS. Foods to avoid in pregnancy.
- NHS. Insomnia.
ጥያቄዎችና መልሶች · 5
የተጠጣው እስከ 8 ሰዓት እንቅልፍ አይሰኝም
የካፌይን ተጽዕኖ ለሰዓታት ሊቆይ ይችላል። ቡናውን ጠዋት ብቻ መጠጣትና መጠኑን መቀነስ ሞክሪ፣ አሁንም እንቅልፍ ካሳጣሽ ካፌይን የቀነሰበት ቡና መምረጥ ይረዳል።
ቡና ያልከው በቀን አንድ ስኒ ብጠጣ ችግር አለው የቡና ሱሰኛ ነኚ
አንድ ስኒ ቡና ለብዙ ጤናማ አዋቂዎች ችግር አያመጣም። ግን የስኒው መጠንና የቡናው ጥንካሬ ይለያያሉ። ልብ መምታት፣ እንቅልፍ ማጣት ወይም የሆድ ምቾት ማጣት ካመጣ መቀነስ ይረዳል።
Enkilf kataw 3month honegh meftihe?
Yeminesubet seat hulgizem and aynet yadergu. Ketiru behuala buna, shay ena koka atetu. Kemeteñat befit silk atayu. Bezih hulet samint sitimokeru kalteshale masmermer yashalal.
ዶክተር እኔግን ቶሎ እቅልፍ አይወስደኝም እዳገበሁ
በየቀኑ በአንድ ሰዓት መነሳት፣ ከሰዓት በኋላ ቡና አለመጠጣትና ከመተኛት አንድ ሰዓት በፊት ስልክ ማስቀመጥ ይረዳል። ከሃያ ደቂቃ በላይ እንቅልፍ ካልመጣ ተነስቶ ደብዘዝ ባለ ብርሃን ትንሽ ቆይቶ መመለስ ይሻላል።
ቡና ስጠጣ ልቤ በጣም ይመታል እረፍት ያሳጣኛል ምን ሁኜ ነው
ይሄ ለካፌይን ስሜታዊ በሆኑ ሰዎች የተለመደ ነው፣ ከደም አይነት ጋር አይገናኝም። በትንሽ ሲኒ፣ ቀጠን አድርጎ፣ ምግብ በልቶ እና ጠዋት ላይ ብቻ መጠጣት ልብ መምታቱን ይቀንሳል።
ተያያዥ ርዕሶች
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
ቃር (ሃርትበርን)
የደም ግፊት
ጭንቀት
ራስ ምታት