በግራ በኩል የሆድ ህመም፦ ጋዝ ብቻ ነው? ጋዝ፣ ሆድ ድርቀትና ዳይቨርቲኩላይቲስ
Left-sided belly pain: is it just gas? Gas, constipation and diverticulitis
በሐኪም (MD) የተጻፈ · Written by an MD · 2026-10-09
ምንድን ነው?
በግራ በኩል የሆድ ህመም ሲኖር ብዙ ሰው "ጋዝ ነው" ብሎ ያልፈዋል። ሎኬሽኑ ፍንጭ ሊሰጠን ይችላል፤ ግን ሎኬሽን (location) ብቻ ዲያግኖሲስ (diagnosis) አይደለም። ከእምብርት በታች በግራ በኩል የኮሎን (colon) የመጨረሻ ክፍል ያልፋል፤ ኮሎን ማለት ትልቁ አንጀት ነው። ስለዚህ ጋዝ፣ ኮንስቲፔሽን (constipation) ማለትም ሆድ ድርቀት፣ እና የኮሎን ግድግዳ ኪሶች መቆጣት (ዳይቨርቲኩላይቲስ፣ diverticulitis) ሁሉም እዚያው ቦታ ህመም ሊያመጡ ይችላሉ።
ጋዝ ከየት ነው የሚመጣው? ስንበላና ስንጠጣ አየር እንውጣለን። በአንጀታችን ያሉ ባክቴሪያዎችም አንዳንድ ያልተፈጩ ካርብስን (carbs) ሲሰባብሩ ጋዝ ያመነጫሉ። ከዚያ በኋላ ብሎቲንግ (bloating)፣ ሆድ መነፋት ወይም ክራምፕ (cramp) ሊሰማን ይችላል። ጋዝ ወይም ሰገራ ከወጣ በኋላ ሪሊፍ (relief) ሊሰማዎት ይችላል፤ ግን መሻሉ ብቻ ጋዝ ብቻ መሆኑን አያረጋግጥም።
ሆድ ድርቀት መፀዳጃ ቤት ስንት ጊዜ ተመላለሱ የሚለው ብቻ አይደለም። ሰገራው ሀርድ (hard) ነው? ሰገራውን ለማውጣት ብዙ መግፋት ያስፈልጋል? ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣ ይሰማዎታል? በየቀኑ ሰገራ ቢወጣም እነዚህ ችግሮች ካሉ ኮንስቲፔሽን ሊሆን ይችላል። የደረቀ ሰገራ በግራው ኮሎን ውስጥ ሲጠራቀም እዚያው ላይ ህመም ይሰጣል።
ዳይቨርቲኩላይቲስ ሌላው ምክንያት ነው። በኮሎን ግድግዳ ላይ ትናንሽ ፓውቾች (pouches)፣ ኪስ የሚመስሉ ቦታዎች፣ ሊፈጠሩ ይችላሉ። መኖራቸው ብቻ ብዙ ጊዜ ሲምፕተም (symptom) አያመጣም። ኢንፍላሜሽን (inflammation)፣ ማለትም መቆጣትና ማበጥ፣ ሲኖር ግን የማይቋረጥ ህመም፣ ትኩሳትና ሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ ሊመጣ ይችላል። ይህ ራሱን የቻለ ሕመም ነው፤ ሙሉውን በዳይቨርቲኩላይቲስ ገጽ ላይ ያንብቡ።
አይ ቢ ኤስ (IBS)፣ የሽንት መንገድ ችግሮች (ኢንፌክሽን፣ የኩላሊት ጠጠር) እና በሴቶች የመራቢያ አካላት ችግሮች (የእንቁላል ከረጢት፣ የወር አበባ ህመም) ተመሳሳይ ህመም ሊያመጡ ይችላሉ። ለዚያ ነው ፓተርኑ (pattern) ከቦታው የበለጠ የሚነግረን።
አደገኛ ምልክቶች
እነዚህ ካሉ ቶሎ ምርመራ ያድርጉ፦
- የማይጠፋ ወይም እየባሰ የሚሄድ ህመም።
- ትኩሳት ከሆድ ህመም ጋር።
- በሰገራ ደም፣ ወይም ጥቁር ሰገራ።
- እርጉዝ ከሆኑ ማንኛውም የሆድ ህመም።
- ማስታወክ የማያቆም፣ ወይም ጋዝም ሰገራም ጨርሶ አለመውጣት ከሆድ መነፋት ጋር።
- ሳያስቡት ክብደት መቀነስ፣ ወይም ከ50 ዓመት በኋላ አዲስ የተጀመረ የሆድ ህመም ከሰገራ ለውጥ ጋር።
ድንገተኛ ወይም ከባድ ህመም፣ ራስን መሳት፣ ወይም ብዙ ደም መፍሰስ ግን ኤመርጀንሲ (emergency) ነው፤ እርዳታ አሁኑኑ ይፈልጉ።
ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?
- ጋዝ ከሆነ፦ ቀስ ብለው ይብሉ፣ ካርቦኔትድ መጠጥና ማስቲካ ይቀንሱ፣ ከምግብ በኋላ ትንሽ ይራመዱ። የትኛው ምግብ እንደሚያነፋዎት (ባቄላ፣ ሽንኩርት፣ ጎመን፣ ወተት) ለሳምንት ይጻፉ።
- ሆድ ድርቀት ከሆነ፦ ፋይበር (fiber) ያለው ምግብ (ሽሮ፣ ምስር፣ አትክልት፣ ፍራፍሬ፣ ሙሉ እህል)፣ በቂ ውሃ፣ በየቀኑ መንቀሳቀስ። የመፀዳዳት ፍላጎት ሲመጣ አያዘግዩ። ከሳምንታት በኋላ ካልተሻለ ፋርማሲ የሚገኝ ፖሊኤቲሊን ግላይኮል (polyethylene glycol) ሊረዳ ይችላል፤ ዝርዝሩ በሆድ ድርቀት ገጽ ላይ አለ።
- ለቀላል ህመም ፓራሲታሞል (paracetamol) መውሰድ ይቻላል። አይቡፕሮፌን (ibuprofen) ያሉ ኤን ኤስ ኤ አይ ዲ (NSAID) መድኃኒቶች ዳይቨርቲኩላይቲስን ሊያባብሱ ስለሚችሉ ለሆድ ህመም አይደጋግሙ።
- ሙቅ ውሃ ጠርሙስ (warm compress) በሆድ ላይ ማድረግ የክራምፕ ህመምን ያቀላል።
- ህመሙን ለሁለት ሳምንት ይከታተሉ፦ መቼ ይጀምራል፣ ምን ያባብሰዋል፣ ምን ያሻሽለዋል። ይህ ለሐኪምዎ ትልቅ መረጃ ነው።
ምልክቶች
ፓተርኑን ይዩ፤ ሐኪምዎም እነዚህን ይጠይቅዎታል፦
- ጋዝ፦ ከምግብ በኋላ ይጀምራል፣ ሆድ ይነፋል፣ ይንቀሳቀሳል፣ ጋዝ ወይም ሰገራ ከወጣ በኋላ ይሻላል፤ መጥቶ ይሄዳል።
- ሆድ ድርቀት፦ የደረቀ ሰገራ፣ ለማውጣት ብዙ መግፋት፣ ሙሉ በሙሉ እንዳልወጣ መሰማት፣ በግራ ታች ያለ ድብርብር ህመም፤ ሰገራ ከወጣ በኋላ ይቀላል።
- ዳይቨርቲኩላይቲስ፦ በግራ ታች የማይቋረጥ ህመም (ሰዓታት ወይም ቀናት ኮንስታንት ሆኖ ይቆያል)፣ ትኩሳት፣ ማቅለሽለሽ፣ የሰገራ ልማድ ለውጥ (ሆድ ድርቀት ወይም ተቅማጥ)፣ ሆዱን ሲነኩት ህመም።
- አይ ቢ ኤስ፦ ለወራት የሚመላለስ ህመምና ሆድ መነፋት ከሰገራ ለውጥ ጋር፣ ከሰገራ በኋላ ይሻላል፤ ትኩሳት ወይም ደም የለም።
- የሽንት መንገድና የመራቢያ አካላት፦ ሲሸኑ ማቃጠል፣ ወደ ጀርባና ወደ ታች የሚወርድ ከባድ ህመም (የኩላሊት ጠጠር)፣ ወይም ከወር አበባ ጋር የተያያዘ ህመም።
ሐኪም መቼ ማየት?
- ከላይ ካሉት አደገኛ ምልክቶች አንዱ ካለ ሳይቆዩ።
- ህመሙ ከሁለት ሳምንት በላይ ከመጣና ከሄደ፣ ወይም ኮንስታንት (constant) ሆኖ ከቀናት በላይ ከቆየ።
- ሐኪሙ ሆድዎን ይመረምራል፣ የደም ምርመራ (ኢንፍላሜሽን ለማየት) እና የሽንት ምርመራ ያዛል። ዳይቨርቲኩላይቲስ ከተጠረጠረ ሲ ቲ ስካን (CT scan) ሊያስፈልግ ይችላል፤ ኪሶቹ ያበጡ መሆናቸውንና ውስብስብ ችግር (እባጭ፣ ቀዳዳ) መኖር አለመኖሩን ያሳያል።
- ቀላል ዳይቨርቲኩላይቲስ ብዙ ጊዜ በእረፍት፣ በፈሳሽ ምግብና በሐኪም የሚወሰን አንቲባዮቲክ (antibiotic) ቤት ውስጥ ይታከማል፤ ከባድ ከሆነ ሆስፒታል ያስፈልጋል።
- ዓመታት የቆየ የሚመላለስ ህመም ከሆነ ኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ሊመከር ይችላል፤ በተለይ ከ45 ዓመት በኋላ ወይም በሰገራ ደም ካለ።
መከላከያ
- በየቀኑ ፋይበር ያለው ምግብ፣ በቂ ውሃና መንቀሳቀስ፤ የደረቀ ሰገራና የኮሎን ግፊት ይቀንሳል።
- ጤናማ ክብደት መያዝና ማጨስ ማቆም የዳይቨርቲኩላይቲስ ስጋትን ይቀንሳል።
- ኤን ኤስ ኤ አይ ዲ መድኃኒቶችን ለረጅም ጊዜ አለመውሰድ።
- የሚያነፋዎትን ምግብ ማወቅና በመጠን መብላት።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- ህመሜ ከጋዝ፣ ከሆድ ድርቀት ወይስ ከዳይቨርቲኩላይቲስ ነው? እንዴት ይለያሉ?
- ሲ ቲ ስካን ወይም ኮሎኖስኮፒ ያስፈልገኛል?
- ለህመሙ የትኛውን መድኃኒት መውሰድ እችላለሁ፣ የትኛውን ልተው?
- ምግቤን እንዴት ልቀይር? ፋይበር ስንት ያስፈልገኛል?
- ዳይቨርቲኩላይቲስ ከሆነ ተመልሶ እንዳይመጣ ምን ላድርግ?
ምንጮች
- NHS. Stomach ache.
- NHS. Bloating.
- NIDDK. Symptoms and Causes of Gas in the Digestive Tract.
- NIDDK. Symptoms and Causes of Constipation.
- NIDDK. Diverticular Disease: Symptoms & Causes.
- NHS. Diverticular disease and diverticulitis.
ጥያቄዎችና መልሶች · 1
Yes, thank you so much. This is helpful.
ተያያዥ ርዕሶች
በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
ዳይቨርቲኩላይቲስ (የአንጀት ኪስ እብጠት)
ሆድ ድርቀት
አይ ቢ ኤስና ሆድ መነፋት
'ጨጓራ አለብኝ' ሲሉ የቱን ማለትዎ ነው? አምስቱ የጨጓራ ችግሮች
አፔንዲሳይቲስ
የኩላሊት ጠጠር