ሕክምናHikimna · Amharic health reference
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ። ለትምህርት ብቻ ነው። Reviewed by a medical professional. Educational only.
1

ቡና፣ ከሰልና እጣን ጭስ ቤት ውስጥ

Buna, charcoal and incense smoke indoors

በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ · Reviewed by a medical professional · 2026-09-20

ምንድን ነው?

ቡና መጠራራት ቤተሰብንና ጓደኛን ያገናኛል፤ ባህሉን መተው አያስፈልግም። ጉዳዩ የምንጠጣው ቡና ሳይሆን፣ የምንተነፍሰው አየር ነው። ከሰል ሲነድ ሁለት ነገሮች ይወጣሉ፦ የጭስ ትንንሽ ፓርቲክሎች (particles) እና ካርቦን ሞኖክሳይድ (carbon monoxide, CO) የሚባል ጋዝ። የእጣን ጭስም…

አደገኛ ምልክቶች

  • የካርቦን ሞኖክሳይድ አላርም ከጮኸ።
  • ከሰል ወይም እጣን በሚነድበት ክፍል ውስጥ ራስ ምታት፣ ማዞር ወይም ማቅለሽለሽ ከመጣ።
  • በክፍሉ ያሉት ሁሉ፣ ልጆችም ጭምር፣ በአንድ ጊዜ ተመሳሳይ ምልክት ካሳዩ። ጉንፋን አንድ ሰው ላይ ይጀምራል፤ ካርቦን ሞኖክሳይድ ሁሉንም በአንዴ ይይዛል።
  • ግራ መጋባት፣ መደንገጥ፣ ወይም ራስን መሳት (passing out)።

ቤት ውስጥ

  • ቤት ውስጥ ከሰል ፈጽሞ አያንድዱ፤ አፓርትመንት፣ ጋራዥ፣ ድንኳን ወይም ተዘግቶ የሚቆይ ማንኛውም ክፍል ውስጥ አይደለም። መስኮት መክፈት ብቻ ሴፍ አያደርገውም።
  • ቡናውን ለቤት ውስጥ በተዘጋጀ ኤሌክትሪክ ማሞቂያ ወይም ስቶቭ (stove) በመመሪያው ያፍሉ።
  • እጣንን ሳያጨሱ መሰብሰብ ይቻላል። ማጨስ ካለብዎ፣ ጥቂት፣ ለአጭር ጊዜ፣ መስኮት ተከፍቶ፣ እና አስም ያለበት ሰው ወይም ሕፃን በክፍሉ ከሌለ ብቻ ይሁን።
  • ከሰል ከቤት ውጭ ከተጠቀሙ፣ ከመስኮት፣ ከበርና ከአየር መግቢያ ርቆ ይሁን፤ ጭሱ ወደ ውስጥ እንዳይገባ።
  • ጋዝ ስቶቭ ካለዎት፣ ወደ ውጭ የሚያወጣ የጭስ ማውጫ (exhaust fan) ይጠቀሙ። EPA።
  • ጄነሬተር (generator) ወይም መኪና ተዘግቶ ባለ ጋራዥ ውስጥ አያስነሱ።
ምልክቶች
  • ራስ ምታት፣ ማዞር፣ ድካምና ድክመት።
  • ማቅለሽለሽ ወይም ማስመለስ፣ የደረት ሕመም።
  • ግራ መጋባት (confusion)፣ ዓይን በደንብ አለማየት፣ ባላንስ (balance) መጠበቅ መቸገር።
  • ምልክቶቹ ጉንፋን ይመስላሉ፤ ግን ትኩሳት የለም። ቤት ውስጥ ይባሳሉ፣ ወደ ውጭ ሲወጡ ይሻላሉ። NHS
  • ከእጣንና ከከሰል ጭስ፦ ሳል፣ የዓይን፣ የአፍንጫና የጉሮሮ መቆጣት፣ አስም (asthma) ያለበት ሰው መተንፈስ መቸገር። EPA
ሐኪም መቼ ማየት?
  • አላርም ከጮኸ ወይም ምልክቶቹ ከመጡ፣ ድንገተኛ እርዳታ ይደውሉ፤ ወደ ውጭ ከወጡ በኋላ ቢሻልዎትም በዚያው ቀን ይመርመሩ።
  • ከቡና ሰዓት በኋላ ደጋግሞ የሚመጣ ራስ ምታት፣ ድካም ወይም ማቅለሽለሽ ካለ፣ ለሐኪምዎ በቡና ጊዜ ከሰል ወይም እጣን እንደሚነድ ይንገሩ።
  • ሕፃናት፣ አረጋውያን፣ እርጉዝ ሴቶች፣ የልብ በሽታ፣ አኒሚያ (anemia) ወይም የመተንፈስ ችግር ያለባቸው ሰዎች በቀላሉ ይታመማሉ፤ ለእነሱ ትንሽ ምልክትም በቁም ነገር ይታይ። CDC
  • አስም ያለበት ልጅ በጭስ ሰዓት ሳል ወይም ማልፋት ካሳየ፣ የአስም እቅዱን ከሐኪሙ ጋር ያድሱ።
መከላከያ
  • በመኝታ ቦታዎች አቅራቢያ፣ በባትሪ የሚሠራ ወይም የባትሪ ባክአፕ ያለው የካርቦን ሞኖክሳይድ ዲቴክተር (CO detector) ይኑር። ባትሪውን በየወቅቱ ይቀይሩ። CDC
  • ባህሉን ይቀጥሉ፤ ማንደጃውን ይቀይሩ። ኤሌክትሪክ ማሞቂያ፣ ንጹህ ነዳጅና ጥሩ የአየር ዝውውር ጭሱን በጣም ይቀንሳሉ። WHO
  • የክረምት ማሞቂያዎን በየዓመቱ በባለሙያ ያስመርምሩ።
  • ቤተሰብና እንግዶች የካርቦን ሞኖክሳይድ ምልክቶችንና «ሁሉም ወዲያውኑ ወደ ውጭ» የሚለውን ሕግ ይወቁ።
  • ስለ ቡና ሥነ ሥርዓት ጭስ የተደረጉት ጥናቶች ትንሽ ናቸው፤ ግን የሚለውን ችላ አንበል፦ የቤት ውስጥ ጭስ ትንሽም ቢሆን ይቀነስ።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
  • በቡና ሰዓት የሚመጣው ራስ ምታቴ ከጭስ ጋር ይያያዛል?
  • ለልጄ አስም የእጣንና የከሰል ጭስ ምን ያህል አደገኛ ነው?
  • ለቤቴ የካርቦን ሞኖክሳይድ ዲቴክተር የት ላስቀምጥ?
  • ለካርቦን ሞኖክሳይድ መመረዝ ምርመራ ወይም ሕክምና ያስፈልገኛል?

የምንጭ ማስታወሻ፦ ከታች ያለው ጽሑፍ የመጀመሪያው ቪዲዮ የምንጭ ስክሪፕት ነው። በስክሪፕቱ ያለው የቴሌግራም ግብዣ የድሮ ነው፤ የአሁኑ የመቀላቀያ ግብዣ አይደለም።

ምንጮች
  • CDC. About Carbon Monoxide Poisoning.
  • EPA. Carbon Monoxide's Impact on Indoor Air Quality.
  • NHS. Carbon monoxide poisoning.
  • WHO. Household air pollution fact sheet.

ጥያቄዎችና መልሶች · 1

hawa…

የሳባ ጤናን ለመጠበቅ የሚርዳ ነገር አሳውቀኝ

ሕክምና

ሳንባን የሚያጸዳ ምግብ የለም። ለሳንባ ጤና ከሁሉ የሚበልጠው ሲጋራና የከሰል፣ የእንጨት ጭስ አለመተንፈስ ነው፤ ከዚያ በየቀኑ መራመድ ወይም ደረጃ መውጣት ሳንባን ያጠነክራል።

ጥያቄዎ ከታየ በኋላ እዚህ ይወጣል። · Your question appears after it is checked.

ተያያዥ ርዕሶች

በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን