ሞሽን ሲክነስ (የጉዞ ማቅለሽለሽ)
Motion sickness
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ · Reviewed by a medical professional · 2026-09-20
ምንድን ነው?
ሞሽን ሲክነስ (motion sickness) በመኪና፣ በአውሮፕላን፣ በጀልባ ወይም በባቡር ጉዞ ላይ የሚመጣ ማቅለሽለሽና ራስ ማዞር ነው። አንጎልዎ እንቅስቃሴን ለማወቅ ከዓይን፣ ከውስጠኛው ጆሮና ከሰውነት የሚመጡ ሲግናሎችን አንድ ላይ ይጠቀማል። በውስጠኛው ጆሮ ውስጥ ቬስቲቡላር ሲስተም…
አደገኛ ምልክቶች
- ድንገተኛ የመራመድ መቸገር፣ ባላንስ (balance) ማጣት ወይም መደናገር።
- ድንገተኛ የአንድ ጎን ፊት፣ እጅ ወይም እግር መደንዘዝ ወይም መዛል።
- በድንገት መናገር ወይም ንግግር መረዳት መቸገር፣ ወይም ድንገተኛ የዓይን ችግር።
- ምክንያት የሌለው ድንገተኛ ከባድ ራስ ምታት።
ቤት ውስጥ
- ፎኑንና መጽሐፉን ለጊዜው ያስቀምጡ። ፊልም ማየትና ሜሴጅ ማንበብ ችግሩን ያባብሳል።
- ወደ ፊት፣ ሩቅ ያለ ቋሚ ነጥብ ወይም አድማሱን ይመልከቱ። እንዲህ ሲያዩ ከዓይንና ከባላንስ ሲስተሙ የሚመጡት ሲግናሎች ይበልጥ ይስማማሉ።
- ተሳፋሪ ሆነው ዓይኖችዎን ጨፍነው ቀስ ብለው ይተንፍሱ።
- መስኮት ከፍተው ንጹሕ አየር ያግኙ።
- በረጅም ጉዞ መሀል ብሬክ ይውሰዱ፤ ውሃ ይጠጡ፣ ትንሽ ይራመዱ።
- ከጉዞ በፊት ከባድ ምግብ፣ ቅመም የበዛበት ምግብና አልኮል ያስወግዱ። ዝንጅብል (ginger) እንደ ሻይ ወይም ብስኩት መውሰድ ለአንዳንዶች ይረዳል። NHS።
- ልጆችን በንግግር፣ በሙዚቃ ወይም በዘፈን ያዘናጉ።
ምልክቶች
- ማቅለሽለሽ፤ አንዳንዴም ማስታወክ።
- ራስ ማዞር።
- ቀዝቃዛ ላብና የፊት መገርጣት።
- ራስ ምታት፣ ድካም ወይም እንቅልፍ መምጣት።
- ምልክቶቹ በድንገት ሊጀምሩና ጉዞው ሲቆም ቀስ ብለው ሊጠፉ ይችላሉ። NHS።
ሐኪም መቼ ማየት?
- ችግሩ በየጉዞው የሚደጋገም ከሆነ፣ ከጉዞ በፊት ፋርማሲስት (pharmacist) ወይም ዶክተር ያማክሩ። የሚረዱ መድኃኒቶች አሉ፤ ከጉዞው በፊት ሲወሰዱ ይበልጥ ይሠራሉ።
- አንዳንድ የሞሽን ሲክነስ መድኃኒቶች እንቅልፍ ያመጣሉ። እንቅልፍ ሲመጣብዎ ድራይቭ ማድረግ አደገኛ ነው። ለልጅ ከመስጠትዎ በፊት ፋርማሲስት ይጠይቁ። CDC Yellow Book።
- ራስ ማዞር ከጉዞ ውጭም ካለ፣ ሌላ ምክንያት ሊኖረው ይችላል። የውስጠኛው ጆሮ ችግር፣ ማይግሬን፣ ዝቅተኛ የደም ግፊት ወይም መድኃኒት ሊሆን ይችላል፤ ቼክ ያስደርጉ።
- ማስታወክ ካልቆመና ውሃ መጠጣት ካስቸገረዎ፣ በተለይ ለልጆችና ለአረጋውያን፣ በቅርቡ ሐኪም ያማክሩ።
መከላከያ
- መኪና ውስጥ የፊት ወንበር፣ ጀልባ ላይ መሀል፣ አውሮፕላን ላይ ከክንፉ አጠገብ ይቀመጡ፤ እንቅስቃሴው እዚያ ያንሳል። MedlinePlus።
- ጉዞ ከመጀመርዎ በፊት ፎኑን ያስቀምጡ፤ ወደ ውጭ ሩቅ ይመልከቱ።
- የሚያልፉ መኪኖችን ወይም ማዕበልን የመሳሰሉ የሚንቀሳቀሱ ነገሮችን አይመልከቱ።
- መድኃኒት የሚያስፈልግዎ ከሆነ፣ ከጉዞው በፊት ይውሰዱ፤ ምልክቱ ከጀመረ በኋላ ብዙም አይሠራም።
- ብዙ ጊዜ ሲጓዙ ሰውነት ቀስ ብሎ ይለምዳል፤ ይህ ከመድኃኒት የበለጠ ውጤታማ መከላከያ ነው። CDC Yellow Book።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- ለረጅም ጉዞ ወይም በረራ የሚረዳኝ መድኃኒት አለ? መቼ ልውሰደው?
- ይህ መድኃኒት እንቅልፍ ያመጣል? ከወሰድኩ በኋላ ድራይቭ ማድረግ እችላለሁ?
- ለልጄ ምን አስተማማኝ ነው?
- ራስ ማዞሬ ከጉዞ ውጭም ስለሚመጣ፣ ሌላ ምክንያት ሊኖረው ይችላል?
የምንጭ ማስታወሻ፦ ከታች ያለው ጽሑፍ የመጀመሪያው ቪዲዮ የምንጭ ስክሪፕት ነው።
ምንጮች
- NHS. Motion sickness.
- MedlinePlus. Motion Sickness.
- CDC Yellow Book. Motion Sickness.
- CDC. Stroke Signs and Symptoms.
ጥያቄዎችና መልሶች · 1
abin…
ከእቅልፍ ትነሳ እያዞረኛል መፍተዉ ነገኝ እባክህን አትለፈኝ
ሕክምና
ከመኝታ ሲነሱ ቀስ ብለው፤ መጀመሪያ አልጋው ጫፍ ላይ ተቀምጠው አንድ ደቂቃ ይቆዩ፣ ከዚያ ይነሱ። ጠዋት ውሃ መጠጣትና ቁርስ አለማሳለፍም ማዞሩን ይቀንሳል።
ተያያዥ ርዕሶች
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
ማይግሬን
ራስ ምታት
የጆሮ ሰም
የስትሮክ ምልክቶችና ፈጣን እርምጃ