የኮሎን ካንሰር ስክሪኒንግ
Colorectal cancer screening
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ · Reviewed by a medical professional · 2026-09-20
ምንድን ነው?
ኮሎን (colon) የትልቁ አንጀት ዋና ክፍል ነው፤ ሬክተም (rectum) ደግሞ መጨረሻው ነው። በውስጣቸው ፖሊፕ (polyp) የሚባል ትንሽ እድገት ሊኖር ይችላል። አብዛኞቹ ፖሊፖች ካንሰር አይደሉም፤ ግን አንዳንዶቹ በጊዜ ሂደት ወደ ካንሰር ሊቀየሩ ይችላሉ። ካንሰር ከመሆናቸው በፊት ሲወገዱ፣…
አደገኛ ምልክቶች
- ብዙ ደም ከፈሰሰ፣ ትልቅ የደም ክሎት (clot) ካዩ፣ ወይም የማይቆም ደም መፍሰስ ካለ።
- ከደም መፍሰስ ጋር ራስን መሳት፣ ማዞር፣ ወይም ከባድ ድክመት ካለ።
- ሰገራው ጥቁር እንደ ሬንጅ ከሆነ ወይም ደም ያለበት ተቅማጥ ካለ፣ በዚያው ቀን አስቸኳይ ምርመራ ይፈልጉ።
ቤት ውስጥ
- ሰገራ ላይ ደም ካዩ፣ «ሄሞሮይድስ (hemorrhoids) ነው» ብለው በራስዎ አይወስኑ። መቼ እንደጀመረ፣ ምን እንደሚመስል፣ እና ሌላ ለውጥ ካለ ይመዝግቡ።
- ቤተሰብዎን ይደውሉና ይጠይቁ፦ ማን የኮሎን (colon) ካንሰር ወይም ፖሊፕ (polyp) ነበረበት? በስንት ዓመቱ? ይህን ለሐኪምዎ ይዘው ይሂዱ።
- የቤት ሰገራ ቴስት ከተሰጠዎ (ለምሳሌ ፊት (FIT))፣ በመመሪያው መሠረት ናሙናውን ሰብስበው በጊዜ ይመልሱ። በየዓመቱ መደገም አለበት።
- የቤት ቴስቱ ፖዚቲቭ ከሆነ፣ ሌላ የቤት ቴስት ደግመው አይሞክሩ፤ ኮሎኖስኮፒ (colonoscopy) ያስፈልጋል።
- ለኮሎኖስኮፒ ቀጠሮ ካለዎት፣ የክሊኒኩን የፕሬፕ (prep) መመሪያ በትክክል ይከተሉ። የሚወስዷቸውን መድኃኒቶች፣ ቫይታሚኖችና ሰፕሊመንቶች አስቀድመው ይንገሩ። ሴዴሽን (sedation) ስለሚሰጥ፣ ወደ ቤት የሚመልስዎትን ሰው አስቀድመው ያዘጋጁ። NIDDK።
ምልክቶች
- ሰገራ ላይ ወይም ውስጥ ደም፤ ቀይ ወይም ጥቁር ሊመስል ይችላል።
- አዲስና የቀጠለ የሰገራ ለውጥ፦ ተቅማጥ፣ ድርቀት፣ ወይም ሰገራው ያልጨረሰ የሚመስል ስሜት።
- የማይጠፋ የሆድ ሕመም፣ ቁርጠት ወይም መነፋት።
- ምክንያቱ ያልታወቀ ክብደት መቀነስ።
- ምክንያቱ ያልታወቀ የአይረን (iron) እጥረት፤ ድካምና ትንፋሽ ማጠር ሊያመጣ ይችላል።
- እነዚህ ምልክቶች ሌሎች ምክንያቶችም አሏቸው። ደም ማየት ሁሉ ካንሰር አይደለም፤ ግን ምክንያቱን የሚያረጋግጠው ሐኪም ብቻ ነው። CDC።
ሐኪም መቼ ማየት?
- ሰገራ ላይ ደም፣ አዲስና የቀጠለ የሰገራ ለውጥ፣ ወይም ምክንያቱ ያልታወቀ የአይረን እጥረት ካለ፣ ቶሎ ያነጋግሩ። 45 እስኪሞላዎት አይጠብቁ።
- 45 ዓመት ከሞላዎትና ስክሪኒንግ ካልጀመሩ፣ በሚቀጥለው ቀጠሮ ይጠይቁ።
- የኮሎን ካንሰር ወይም ፖሊፕ የፋሚሊ ሂስትሪ፣ ወይም የአንጀት እብጠት በሽታ (inflammatory bowel disease) ካለዎት፣ ስክሪኒንግ ከ45 በፊት ሊያስፈልግ ይችላል፤ ሐኪምዎ ይወስናል። CDC።
- የቤት ሰገራ ቴስት ፖዚቲቭ ከሆነ፣ ኮሎኖስኮፒ ለመያዝ ቶሎ ይደውሉ። ፖዚቲቭ ማለት ካንሰር ተረጋግጧል ማለት አይደለም፤ ግን ምርመራው መጠናቀቅ አለበት።
- ስለ ሰገራ ለመናገር ካፈሩ፣ በግል ለመወያየትና በሚመችዎ ቋንቋ ኢንተርፕሪተር (interpreter) ይጠይቁ። የሥራ ሽፍት ወይም ኮስት ካስቸገረ፣ ከክሊኒኩ ጋር ፕላን ያድርጉ።
መከላከያ
- በጊዜው ስክሪኒንግ ማድረግ ዋናው መከላከያ ነው። ፖሊፕ ካንሰር ከመሆኑ በፊት ሲወገድ ካንሰሩ ይከላከላል።
- የስክሪኒንግ ኦፕሽኖች (options)፦ የቤት ሰገራ ቴስት (FIT) በየዓመቱ፣ ወይም ኮሎኖስኮፒ ለከፍተኛ ሪስክ ለሌለው ሰው በየ10 ዓመት። ሌሎችም አሉ፤ የትኛው እንደሚስማማዎት ከሐኪምዎ ጋር ይምረጡ። CDC።
- ሲጋራ አያጨሱ፣ አልኮል ይቀንሱ፣ ጤናማ ክብደት ይጠብቁ፣ ሰውነትዎን ያንቀሳቅሱ።
- ልጆችዎም እንዲያውቁ፣ የቤተሰብዎን የካንሰር ታሪክ ጽፈው ያስቀምጡ።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- የኮሎን ካንሰር ስክሪኒንግ ያስፈልገኛል? መቼ ልጀምር?
- በቤተሰቤ ታሪክ ምክንያት ቀድሜ ወይም በተደጋጋሚ ልመረመር ይገባል?
- ለእኔ የቤት ሰገራ ቴስት ወይስ ኮሎኖስኮፒ ይሻላል? ኮስቱና ኢንሹራንሱ እንዴት ነው?
- ሰገራዬ ላይ ያየሁት ደም ምክንያቱ ምንድን ነው? ተጨማሪ ምርመራ ያስፈልጋል?
የምንጭ ማስታወሻ፦ ከታች ያለው ጽሑፍ የመጀመሪያው ቪዲዮ የምንጭ ስክሪፕት ነው። በስክሪፕቱ ያለው የቴሌግራም ግብዣ የድሮ ነው፤ የአሁኑ የመቀላቀያ ግብዣ አይደለም።
ምንጮች
- CDC. Screening for Colorectal Cancer.
- USPSTF. Colorectal Cancer: Screening.
- NHS. Bowel cancer: Symptoms.
- NIDDK. Colonoscopy.
ጥያቄዎችና መልሶች
የመጀመሪያውን ጥያቄ ይጠይቁ።
ተያያዥ ርዕሶች
በሕክምና ባለሙያ የተገመገመ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
'ጨጓራ አለብኝ' ሲሉ የቱን ማለትዎ ነው? አምስቱ የጨጓራ ችግሮች
የብረት ማሟያን በደህና መውሰድ
የተለመዱ የሕክምና ምርመራዎችን መረዳትና ለክሊኒክ ጉብኝት መዘጋጀት
የማኅጸን ጫፍ ካንሰር ምልክቶችና የምርመራ ሂደት