አርትራይተስ፦ ሁሉ አንድ አይደለም
Arthritis: osteoarthritis and rheumatoid arthritis
በሐኪም (MD) የተጻፈ · Written by an MD · 2026-10-15
ምንድን ነው?
አርትራይተስ (arthritis) ሁሉ አንድ አይደለም። ጆይንት ማለት ሁለት አጥንቶች የሚገናኙበት ቦታ ነው። በዚህ ቪዲዮ ከብዙ ዓይነቶቹ ሁለቱን እናያለን።
ኦስቲዮአርትራይተስ (osteoarthritis) በጆይንቱ ውስጥ ያሉ ቲሹዎች ቀስ በቀስ ሲጎዱ ይከሰታል። ካርቲሌጅ፣ የአጥንቶችን ጫፍ የሚሸፍነው ለስላሳ ቲሹ፣ ከእነዚህ አንዱ ነው። ዕድሜ ብቻ አይወስነውም፤ የቀድሞ የጆይንት ጉዳትም ሪስኩን ይጨምራል።
ሩማቶይድ አርትራይተስ (rheumatoid arthritis) ደግሞ ኢሚዩን ሲስተሙ የራሱን ጆይንቶች የሚያጠቃበት ኦቶኢሚዩን በሽታ ነው።
አደገኛ ምልክቶች
- አንድ ጆይንት በድንገት በጣም ካመመ፣ ካበጠና ከሞቀ፣ ትኩሳት ባይኖርም አስቸኳይ ምርመራ ያድርጉ። ኢንፌክሽን ሊሆን ይችላል።
ቤት ውስጥ ምን ማድረግ?
- እንደ መራመድና ስዊሚንግ (swimming) ያሉ በጆይንት ላይ ከባድ ጫና የማያደርጉ እንቅስቃሴዎችን በትንሹ ይጀምሩ።
- ጡንቻን ማጠናከርና ፊዚካል ቴራፒ ሊረዱ ይችላሉ። ሕመሙ በጣም ከጨመረ አይግፉ፤ ፕሮግራሙን ከፊዚካል ቴራፒስት ጋር ያስተካክሉ።
- ከመጠን በላይ ውፍረት ካለ፣ መቀነስ በጉልበት ላይ ያለውን ጫና ይቀንሳል።
ምልክቶች
- ሕመም፣ እብጠትና መገተር የተለመዱ ምልክቶች ናቸው።
- በኦስቲዮአርትራይተስ ሕመሙ ብዙ ጊዜ በእንቅስቃሴ ይጨምራል፤ የጠዋት መገተሩም በአጭር ጊዜ ይለቃል።
- በሩማቶይድ አርትራይተስ የሁለቱም እጆች ጣቶች ሊያብጡ፣ መገተሩም ከግማሽ ሰዓት በላይ ሊቆይ ይችላል።
- እነዚህ ፍንጭ ናቸው፤ ዳያግኖሲስ ግን ምርመራ ይፈልጋል።
ሐኪም መቼ ማየት?
- የሚቀጥል እብጠት ካለ፣ ዕድሜ ነው ብለው ችላ አይበሉ።
- የትኞቹ ጆይንቶች እንደሚያሙ፣ መገተሩ ምን ያህል እንደሚቆይ፣ እብጠት እንዳለና ሕመሙ መቼ እንደሚጨምር ለዶክተርዎ ይንገሩ።
- ለሩማቶይድ አርትራይተስ ፔይንኪለር (painkiller) ብቻ አይበቃም፤ የጆይንት ጉዳትን የሚቀንስ ሕክምና ቀድሞ መጀመር ያስፈልጋል።
ለሐኪምዎ የሚጠይቋቸው
- የጆይንት ሕመሜ ምክንያት ምንድን ነው? ምን ምርመራ ያስፈልጋል?
- ለእኔ የሚስማማው የእንቅስቃሴ ፕሮግራም ምንድን ነው?
- ሕመምን ከማስታገስ በተጨማሪ የጆይንት ጉዳትን የሚቀንስ ሕክምና ያስፈልገኛል?
ምንጮች
- NIAMS. Osteoarthritis. https://www.niams.nih.gov/health-topics/osteoarthritis
- NIAMS. Osteoarthritis: Diagnosis, Treatment, and Steps to Take. https://www.niams.nih.gov/health-topics/osteoarthritis/diagnosis-treatment-and-steps-to-take
- NIAMS. Rheumatoid Arthritis. https://www.niams.nih.gov/health-topics/rheumatoid-arthritis
- NIAMS. Rheumatoid Arthritis: Diagnosis, Treatment, and Steps to Take. https://www.niams.nih.gov/health-topics/rheumatoid-arthritis/diagnosis-treatment-and-steps-to-take
- NHS. Septic arthritis. https://www.nhs.uk/conditions/septic-arthritis/
ጥያቄዎችና መልሶች
የመጀመሪያውን ጥያቄ ይጠይቁ።
ተያያዥ ርዕሶች
በሐኪም (MD) የተጻፈ። ለትምህርት ብቻ ነው፤ የግል የሕክምና ምክር አይደለም። ድንገተኛ ችግር ካለ 911 (አሜሪካ) ወይም 907 (አዲስ አበባ)።
ሁሉም ጽሑፎች · ስለ እኛ · ያግኙን
ሪህ (ጋውት)
ለልብና ለስኳር በሽታ መከላከያ የአካል እንቅስቃሴ
የተለመዱ የሕክምና ምርመራዎችን መረዳትና ለክሊኒክ ጉብኝት መዘጋጀት